
በህትመት ጭብጥ ካናዳዊ ምዝገባ
ዋናው የምዝገባ ርእስ
ስድብ በማንኛውም ቋንቋ ስህተት ነው
Main entry under title :
Abuse is wrong in any language
በተጨማሪ የቀረበ /የመጣ/ በፈረንሳይኛ ቋንቋ በርዕስ
ላቭዩላንስ ኤ አናክሴንታብል ፐ አንፓርት ላ ላንግ
አይኤስቢኤን 978-0-662-03028-7
ካታ.ቁ.ጄ2-131/2008Am
ኤችቪ6623.23ሲ3ኤ38 1995 362.829’2’ 0971 ሲ95-980093-ኤክስ
ይህ የመንግስት ህጋዊ ትምህርትና መረጃ ፕሮጀክት በፍትሕ መምሪያ በቤተሰብ ትንኮሳ መነሻ ስር የቀረበ ነው፡፡
በካናዳ ፍትህ ሚኒስትርና ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ስልጣን ታትሟል
በካናዳ ፍትሕ መምሪያ
ኦታዋ ፣ ኦንታሪዮ
ኬ1ኤ 0ኤች8
ጄዩኤስ-677ኢ
© የስራና የመንግስት ሙያዊ አገልግሎት ሚኒስተር ካናዳ 2008
በካናዳ ታተመ
ነገሩ በትክክለኛ ቅጂ ከቀረበና ለስራው ምንጭ ምስጋና እስከተካተተ ድረስ ፣ ይህን አነስተኛ መፅሐፍ ያለፍትህ መምሪያ ፍቃድ ፎቶ ኮፒ ማድረግ ይቻላል፡፡ ነገሩን ለማንኛውም በሌላ ይዞታና አቀራረብ ለመቀጠል የመምሪያው የፅሁፍ ፈቃድ ያስፈልጋል፡፡
(Amharic/Amharique)
የፍትሕ መምሪያ የኒው ብሩንስዊክ የመንግስት የህግ ትምህርትና መረጃ አገልግሎት ረቂቅ ህትመታቸው የዚህች አነስተኛ መፅሐፍ መሰረት ሆኖ እንዲያገለግል በመፍቀዳቸው ሊያስመሰግን ይወዳል፡፡
የፍትህ መምሪያ፣ በተጨማሪ የፒኤልኢአይ ኒትወርክ፡፡ የፍትህ መምሪያዎችና ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የጠቅላይ ግዛትና አካባቢያዊ የስራ ባልደረቦች የካናዳ ዜጎችና ኢሜግሬሽን፣ የካናዳ ቅርፅ መምሪያ ፣ የካናዳ ጤና ፣ የካናዳ የሰው ኃይልና ልማት አጠቃላይ የካናዳ ጠበቆች በካናዳ የሴቶች ሁኔታ /ጥ.ማ. የመምሪያዎቹ ስሞች በመዋጮ ጊዚያቸው የተዘረዘሩ ናቸው/፡፡ በተጨማሪም ሊያመሰግን ይወዳል፡፡
ይህ አነስተኛ መፅሐፍ በመላ ካናዳ የብሔር ብሔረሰብ የባህል ቡድኖችና የማህበረሰብ ቡድኖች አባላት ጋር በመካከል የበለፀገ ነው፡፡ በዚህ ዝግጅት ላይ የተሳተፉትን በሙሉ ስላደረጉት እርዳታ እያደነቅን ፣ ስለጠቃሚው አስተዋፅኦዋቸው እናመሰግናቸዋለን፡፡
ይች አነስተኛ መፅሐፍ በቤተዘመድ ወይም በቤተሰብ ውስጥ አግባብ በመጎሳቆል ላይ የሚገኙትን ስደተኛ ወይም ተፈናቃይ ሴቶች ሁኔታ የሚገልፅ ነው፡፡ ጉስቁልና እየደረሰባት ያለች ሴት ካወቃችሁ ይህችን አነስተኛ መፅሐፍ ስጧት፡፡ ርዳታ ትፈልግ እንደሆነ ጠይቋት፡፡ የእናንተን ድጋፍ ልትፈልግ ትችላለች ብቻዋን አለመሆኗን አሳውቋት፡፡
ይች አነስተኛ መፅሐፍ ስለስደተኞች ፣ ስለተፈናቃይ ፣ ሴቶች የተፃፈች ብትሆንም እንኳን ለወንዶችም ቢሆን ማጎሳቆል በተመሳሳይ መልኩ ስህተት ነው፡፡ ማንም ጉስቆልና እየደረሰበት ያለ ሰው ዕርዳታ ለማግኘት ይበረታታል፡፡
እንደ ስደተኛ ወይም ተፈናቃይ ሴት ብቸኝነት ይሰማችኋል፡፡ ከሰዎች ጋር የመነጋገር ችግር ሊኖርባቸው ይችላል፡፡ እየተጎሳቆላችሁ ከሆነ ስለራሳችሁ ወይም ስለልጆቻችሁ ልትፈሩ ትችላላችሁ፡፡
ጉስቁልና እየደረሰባችሁ ባለበት ወቅት ስለካናዳ ህግ ፣ ስለመብቶቻችሁ ልታገኙት ስለምትችሉት እርዳታ በይበልጥ ለማወቅ ልትሹ ትችላላችሁ፡፡
በአስቸኳይ ወቅት
ከቻላችሁ ፖሊስ ወይም ጓደኛ በስልክ ጥሩ፡፡
ሌላ ሰው እንዲያያችሁ ወደ ውጭ ሩጡ / የበለጠ ደህና ነኝ ብላችሁ ካሳሰባችሁ/፡፡
ጩሁ ፖሊስ በስልክ እንዲጠሩ ጎረቤቶች ይሰሙ፡፡
አንድ ሰው በሚጎዳችሁ ወይም በመጥፎ መንገድ በሚይዛችሁ ወቅት ተጎሳቁላችኋል፡፡
ማጎሳቆሉ አካላዊ ጾታዊ ፣ ስሜታዊ ስነልቦናዊ ገንዘብ ነክ ሊሆን ይችላል፡፡ ከአንድ በላይ መጎሳቆል ሊያጋጥማቸሁ ይችላል፡፡
ባብዛኛው አጎሳቋዩ የትዳር ጓደኛ፣ የቀድሞ የትዳር ጓደኛ፣ ተጓዳኝ ወይም የቀድሞ ተጓዳኛ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ አጎሳቋይ የቤተሰባችሁ አባል ወይም የትዳር ጓደኛችሁ ወይም የተጓዳኛችሁ ቤተሰብ ነው፡፡ አጎሳቋዩ ወንድ ወይም ሴት ሊሆን ይችላል፡፡
የአካል መጎሳቆል ምሳሌዎች የሚከተሉትን ያካትታል፡-
በካናዳ ይህን ዓይነቶቹ ጥቃቶች ወንጀሎች ናቸው፡፡
የፆታ ጥቃት እናንተ በማትስማሙበት ጊዜ ፆታዊ መንካት ወይም ፆታዊ ድርጊት ነው፡፡
ይህም በካናዳ ውስጥ ወንጀል ነው፡፡
ስሜታዊ ወይም ስነልቦናዊ ጥቃት የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል፡፡
በካናዳ እነዚህ ወንጀሎች ናቸው፡፡
ጥቂት ከገንዘብ ነክ ማጎሳቆል ምሳሌዎችየሚከተሉት ያካትታል፡፡
በካናዳ እነዚህ ወንጀሎች ናቸው፡፡
የአንዳንድ የትንኮሳዎች ዓይነቶች ወንጀል ተደርገው ባይቆጠሩም እንኳን ስህተት ስለሆኑ ማንም በእናንተ ላይ ለማድረግ መብት የለውም፡፡ ጥቂቶቹ ምሳሌዎችም ፣
ሊረዷችሁ የሚችሉ ሰዎች አሉ፡፡
ስደተኞችና ተፈናቃዮችን ለሚያገለግለው የብዙ ባህል ማህበርና ወይም ቡድን በስልክ ጥሩ፡፡ ምን ዓይነት እርዳታ ልታደርጉ እንደምትችሉ እወቁ፡፡ የት ሌላ ጥሪ እንደምታደርጉ ወይም ለእርዳታ እንደምትሄዱ ጠይቋቸው፡፡
ፖሊስ ጥሩ እነርሱ እናንተንና ልጆቻችሁን ይጠብቃሉ፡፡
የሚከተሉትንም ሊያስገኙላችሁ ይችላሉ፡፡
ለመቆየት ከፈለጋችሁም እርዳታ ልታገኙ ትችላላችሁ፡፡
ማጎሳቆል በማናቸውም ቤተሰቦች ውስጥ ሊሆን ይችላል፡፡ በካናዳ ዜጎችና በስደተኞች ላይ ይሆናል፡፡ ልጆች ባሏቸውና ልጆች በሌሏቸው ባለፀጋ ወይም ደሃ ባለሙያና እቤት በሚውሉ እናቶች እንዲሁም በወጣቶች በትልልቆች ላይ ይደርሳል፡፡ ልዮ ልዮ ሃይማኖት ፣ዘር፣ ባህልና ጎሣ ባላቸው ሴቶች ላይ በሙሉ ይደርሳል፡፡ ማጎሳቆል በማንኛውም የግንኙነት ደረጃ ሊደርስ ይችላል፡፡
ስለጉስቁልና መናገር ሊከብድ ይችላል፡፡ መጎሳቆል የደረሰባቸው ብዙ ሴቶች ያፍራሉ ወይም ቤተሰባቸውና ጓደኞቻቸው አያምኑንም በማለት ይፈራሉ ነገር ግን አስታውሱ ምንም የምታደርጉት ነገር ማንም ሰው እንዲጎሳቁላችሁ መብት አይሰጠውም፡፡ ለማጎሳቆል ሰበብ የለም የእናንተን ስህተት አይደለም፡፡
ብዙ ሴቶች ማጎሳቆል የአዙሪት ፀባይ እንዳለው ደርሰውበታል፡፡ አጎሳቋይ የሃይልን እርምጃ ለመውሰድ እስኪደርስ ድርስ ውጥረቱ ለጥቂት ጊዜ እየጋለ ይመጣል፡፡ ነገር ከፈነዳ ወይም ከሃይለ ድርጊቱ በኃላ የዝምታ ወይንም የፀጥታ ጊዜ አለ፡፡ አጎሳቋይ አዝናለሁ ብሎ ነገሩ ሁለተኛ እንደማይደገም ቃል ሊገባ ይችላል፡፡ ነገር ግን በዚህ ጊዜ ውስጥ ውጥረቱ ይጨምርና አጎሳቋይ እንደገና ሃይለኛ ሊሆን ይችላል፡፡ የማጎሳቆል አዙሪት ይቀጥላል፡፡

በአንድ ወላጅ ላይ ጥቃት ሲደርስበት ማየት ወይም መስማት ለልጆች በጣም ከባድ ነው፡፡ ይህ በሕጻኑ ሁለተናዊ እንቅስቃሴ ማለትም አካላዊና አእምሮአዊ ጤንነት፣ በራስ- ክብር እና በትምህርት ክትትል ላይ ተፀዕኖ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ሕጻኑ ከሌሎች ጋር በሚኖረው ማህበራዊ ግንኙነት ሂደት ላይም ተፅዕኖ ሊያደርግ ይችላል፡፡ በቤተሰቦቻቸው ውስጥ ማጎሳቆልን ሲመለከቱ ያደጉ ወንዶች ልጆች በሚያድጉበት ጊዜ የራሳቸውን የትዳር ጓደኛ ወይም ተጓዳኝ ለማጎሳቆል የበለጠ ዝንባሌ ይኖራቸዋል፡፡ ልጃገረዶች በሚያድጉበት ጊዜ በግንኙነቶቻቸው ወቅት ማጎሳቆልን እንደሕይወት እውነታ ለመቀበል የበለጠ ዝንባሌ ይኖራቸዋል፡፡
እንደወላጅ፣ የጥቃት ሰለባ መሆን ደግሞ የራሳችሁን ልጆች ለመንከባከብ ከባድ ይሆንባቸዋል፡፡ ልጆቹ ጥቃት አድራጊውን እየተመለከቱ ለእናንተ አክብሮት መስጠት እንደሌለባቸው ይማራሉ፡፡ ጥቃቱ በተጨማሪ ለልጆቻችሁ የምታጋሩት ጥቂት ኃይል እስኪቀራችሁ ድረስ ይሸረሽራችኋል፡፡
ጥቃት አድራሹ በተጨማሪ ልጆቻችሁን እያጠቃ ከሆነ፣ እርዳታ ልታገኙላቸው ይገባል፡፡ የሕጻን ጥቃት ከሕግ ተፃፃሪ ነው፡፡ ምክር፣ዕርዳታ ወይም ሙያዊ ምክር ለማግኘት ወደ ሕጸናት በጎ አድራጎቶት ወይም የቤተሰብ ሙያዊ አገልግሎት ኤጀንሲ ልትሄዱ ትችላላችሁ፡፡ ሕጻናት ከጥቃት መጠበቅ ያስፈልጋቸዋል፡፡
በመጀመሪያ ስለራሳችሁና ስለልጆቻችሁ ደኅንነት ማሰብ ይገባችኋል፡፡ ስፍራውን ከተውንቤተሰባችን ወይም ጓደኞቻችን ለወደፊት አይረዱንም ብላችሁ ልትፈሩ ትችላላችሁ፡፡ ይህ ሊሆን ይችላል፡፡ ቢሆንም አንኳን ግን ለእናንተና ለልጆቻችሁ በጥቃቱ ውስጥ ከመቆየት ይልቅ የተሻለ ሊሆን ይቸላል፡፡
ለአጭር ወይም እንዲያውም እስከ እስከመጨረሻው መተውን ልትመርጡ ትላላችሁ፡፡ ሁለቱም ምርጫዎች ጋብቻችሁን ወይም ግንኙነታችሁን ማቋረጥ አለባችሁ ማለት አይደሉም፡፡ ውሳኔዎቻችሁን በምታደርጉበት ጊዜ የሚከተሉትን አሰላስሉ፡፡
መቆየት እንደሚሻላችሁ ልትወስኑ ትችላላችሁ፡፡
ብትጎዱ አሁንም የሕክምና እርዳታ ማግኘት ይገባችኋል፡፡ጉዳቶቹን ያደረሰውን ሰው ማንነት ለማንም መንገር የለባችሁም፡፡ ለዶክተራችሁ በትክክል ምን እንደሆነ ብትነግሩት ለሕክምናችሁ የተሻለ ነው፡፡
ስለጉዳቶቻችሁና ጥቃታችሁ የደረሱባችሁን ጊዜያት በማስታወሻ ወይም በዕለት ሁኔታ መመዝገቢያ ላይ መመዝገብ በኋላ ለመልቀቅ ብትወስኑ ሊረዳችሁ ይችላል፡፡ በፍጥነት ቦታውን ለመልቀቅ ካስፈለጋችሁ የተዘጋጀ ዕቅድ መያዝ ጥሩ አሳብ ነው፡፡
የመጀመሪያዎቹ የስልክ መዝገብ ጥቂት ገጾች የፖሊስንና ሌሎች የአደጋ ጊዜ ሙያዊ አገልግሎት መስሚያዎችን ዝርዝር ሊጽፉ ይችላሉ፡፡ ምናልባት ርዳታቸውን ብትፈልጉ የፖሊስ የጽሕፈት ቤትን ቁጥር ማወቅ ጥሩ አሳብ ነው፡፡ በአደጋ ጊዜ 911 ለመደወልም ትችላላችሁ፡፡
ሊረዷችሁ የሚችትን ሰዎች አድራሻዎችና ስልክ ቁጥሮች የመሳሰሉትን መረጃዎች አሰባስቡ፡፡ ከቻላችሁ ጥቂት ገንዘብ ቆጥቡ፡፡
የተሻለ ስሜት የሚያስገኝላችሁን ነገሮች ለመሥራት ሞክሩ፡፡ ሙያዊ ምክር ለማግኘት ወይም አዲስ የስራ ችሎታ ለመማር ትችላላችሁ፡፡ ሊረዷችሁ የሚችሉ ጓደኞች ወይም የቤተሰብ አባላት አፈላልጉ፡፡
አጥቂው አድራጎቱን ለመለወጥ ከፈለገ ሙያዊ ምክር ሊያገኝ ይችላል፡፡ በረጅም ጊዜ ርዳታ አንዳንድ አጥቂዎች ድርጊታቸውን ማቆምን ተምረዋል፡፡ ቀደም ሲል ኃይል ሲጠቀሙ የቆዩትን ሰዎች ለመለወጥ ግን በጣም ከባድ ነው፡፡ ጥቂቱ በጊዜ ሂደት እየተበላሸ ይሄዳልና፡፡
ዘለፋ ያለበትን አካባቢ ብትተውም እንኳን ስለልጆቻችሁ ጥበቃ ልታመለክቱ ትችላላችሁ፡፡
ልጆቻችሁ በአደጋ ውስጥ ናቸው ብላችሁ ካሰባችሁ በምትለቁበት ጊዜ አብራችሁ ይዛችኋቸው ሂዱ፡፡ ወዲያውኑ ለፍርድ ቤት የጥበቃ ትዕዛዝ እንዲያስተላልፉ አመልክቱ፡፡ ጠበቃ ሊረዳችሁ ይችላል፡፡ ጠባቃችሁ የልጆቻችሁ አባት ለእናንተና ለልጆቻችሁ የገንዘብ ድጋፍ እንዲከፍል ፍርድ ቤቱን እንዲያዝ በመጠየቅ ሊረዳችሁም ይችላል፡፡ ፍርድ ቤቱን ውሳኔውን ለልጆቹ በጣም በሚስማማ ነገር ላይ ይመሠርታል፡፡
የልጆቹን አሳዳጊነት ካገኛችሁ አባታቸው ሊጎበኞአቸው ይችላል፣ የሚል አዝማሚያ ይኖራል፡፡ አባትዬው ልጆቹን በሚወስድበትና በሚመልስበት ጊዜ ሌላ ሰው እዚያ እንዲኖር ለማድረግ ትፈልጉ ይሆናል፡፡ ስለልጆቻችሁ ደህንነት የምትጨነቁ ከሆነ፣ ጠበቃችሁ ፍርድ ቤቱ አንድ ሌላ ሰው ጉብኝቶቹን እንዲቆጣጠር እንዲያዝ ሊጠይቅ ይችላል፡፡
የልጆቻችሁ አባት ወይም ሌላ ሰው ልጆቹን ከአገር ውጭ ሊወስዳቸው ነው ብላችሁ ካሰባቹህ ይህንኑ ለጠበቃችሁ ንገሩት፡፡ ከጠየቃችሁ፣ ፍርድ ቤቱ የልጆቹ ፓስፖርቶች በፍርድ ቤት እንዲጠበቁ ሊያዝ ይችላል፡፡
ልጆቻችሁ የካናዳ ዜጎች ከሆኑ ፓስፖርት ጽሕፈት ቤት በስልክ አገልግሎት በስ.ቁ. 1-800-567-6869 ወይም ቲቲ ዋይ ሙያዊ አገልግሎት በስ.ቁ. 1-866-255-7655 ይደውሉ፡፡ ምናልባት አንድ ሰው አንድ ፓስፖርት ሊያገኝላቸው ሞክሮ ልትጠሩት እንድትችሉ ልጆቹን ሥሞች በዝርዝር ውስጥ እንዲጨምሩት ጠይቋቸዋል፡፡ ልጆቻችሁ ሌላ ዜግነት ካላቸው፣ ለልጆቻቸሁ ፓስፖረት እንዲከለክሏቸው እንዲጠይቋቸው ኢንባሲውን ወይም ቆንስላውን አነጋግሩ፡፡
የማሳደግ ትዕዛዝ ካላችሁ ምናልባት ችግር ካለ ቅጂውን ለልጆቻቹህ ትምህርት ቤት መስጠቱ ጥሩ አሳብ ነው፡፡
የካናዳ ዜጎች ወይም ቋሚ ነዋሪዎች የበደል አካባቢን በመልቀቃችሁ ከካናዳ ልትወገዱ አትችሉም፡፡ ቋሚ ነዋሪ አንዳንድ ጊዜ ቋሚ ስደተኛ ተብሎ ይጠራል፡፡የካናዳ ዜጋ ወይም ቋሚ ነዋሪ መሆናችሁን ካላወቃችሁ፣ የአካባቢያችሁን የዜግነት ጉዳይ ጽሕፈት ቤት በስልክ ጠይቁ፡፡ በስልክ መዝገብ ካሉ ሰማያዊ ፔጅስ ዜግነትና ስደተኝነት ርዕስ ሥር ተመልከቱ፡፡
ስደተኛ ሆናችሁ ከተገኛችሁ ወይም ጥበቃ የሚፈልግ ዓይነት ከሆናችሁ ቋሚ ነዋሪ ለመሆን በራሳችሁ ልታመለክቱ ትችላላችሁ፡፡ ከጥገኛ ስደተኞች ወይም ጥበቃ ከሚፈልጉ አንዱ ሆነው ለሁለታችሁም ቋሚ ነዋሪነት ለማመልከት በሂደት ላይ ከሆናችሁ ማመልከቻችሁን ልትተዉ ከበዳያችሁ ክስ ጋር በተያያዘ የስደተኛ ጥበቃ ክስ አቅርባችሁ ከነበረ የእናንተው እንዲለይ ልትጠየቁ ትችላላችሁ፡፡ በዚህ ሁኔታ፣ በሰብዓዊና በርህራሄ ምክንያት ለቋሚ ነዋሪነት ልታመለክቱ ካናዳ ውስጥ ለምን መቆየት እንደሚገባችሁ በግልጽ ማሳወቅ ቢኖርባችሁም ይህ የሚሳካላችሁ ስለመሆኑ ዋስትና የለም፡፡
ከበዳያችሁ ክስ ጋር ተያይዞ የስደተኛ ጥበቃ ክስ አቅርባችሁ ከነበረ የእናንተው እንዲለይ ልትጠይቁ ትችላላችሁ፡፡ አሊያም የራሳችሁን ቃል በመስጠት የግላችሁን ውሳኔ ታገኛላችሁ፡፡
የሕግ ምክር ለማግኘት ትፈልጉ ይሆናል፡፡ አንዳንድ እንዲረዳችሁ የምትከፍሉት ከሆነ ይህ ሰው ጠበቃ፣ በጠበቃ ቁጥጥር ሥር ያለ የሕግ ተማሪ፣ የኩቤክ የሕዝብ ውል አዋዋይ ክፍል አባል፣ ወይም በካናዳ የኢሚግሬሽን ሙያዊ አማካሪዎች ማኅበር አባል መሆን አለበት፡፡ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ለአካባቢው ካናዳ የኢምግሬሽን ማዕከል ስልክ ይደውሉ፡፡ በስልክ መዝገብ ካሉ ሰማያዊ ፔጅስ ዜግነትና ስደተኝነት ርዕስ ሥር ተመልከቱ፡፡
የአሳዳጊነት ስልጣን እንደተሰጠው፣ማሳደጋችሁ ስለተቋረጠ ብቻ ከካናዳ አትወገዱም፡፡ (ስለገንዘብ ድጋፍን በተጨማሪ ተመልከቱ) ፡፡
በዳዩ ቢያጠቃችሁ ወይም ለወደፊት አደርገዋለሁ ካለ፣ ፖሊስ ድርጀት ስልክ ልትደውሉ ትችላላችሁ፡፡ ከፖሊስ ድርጅትም ሊረዷችሁ ይመጣሉ፡፡ ብዙዎቹ የፖሊስ መኮንኖች በቤተሰቦችና ዘመዶች የሚነሳውን በደል እንዴት እንደሚቆጣጠሩ ሠልጥነዋል፡፡ የሕክምና እርዳት ካስፈለጋችሁ ወደሆስፒታል ሊወስዷችሁ ወይም በደህና እንደትለቀቁ ሊረዷችሁ ይችላሉ፡፡
በአካባቢያችሁ መጠለያ ካለ ወደዚያ ልትሄዱ ትችላላችሁ፡፡ ይህ እናንተና ልጆቻችሁ ለጥቂት ቀናት ወይም ሣምንታት በደህና ልትቆዩበት የምትችሉበት አስተማማኝ ሥፍራ ነው፡፡ በገንዘብ ምንጮቻችሁ ላይ ተመሥርቶ፣ ለቆይታችሁ በከፊል እንድትከፍሉ ልትጠየቁ ትችላላችሁ፡፡
የመጠለያው ሠራተኞችና በጎ ፈቃደኞች የእርዳታና መረጃ ይሰጠችኋል፡፡ የምትፈልጉት ይህ ከሆነ፣ የሕግ ምክር፣ የገንዘብ እርዳታና አዲስ የሞኖሪያ ሥፍራ እንድታገኙ ሊረዷችሁ ይችላሉ፡፡ለማምጣት ጊዜ ካልነበራችሁ ምግብ ፣ ልብስ፣ ዳይፐርና አሻንጉሊትም ደግሞ አሏቸው ለበዳዩ የት እንዳላችሁ ይነግሩታል፡፡
መጠለያዎች በማሕረሰብ ቡድኖች የሚካሄዱ ናቸው፡፡ የስልክ ቁጥሮቻቸው ብዙውን ጊዜ ከሌሎች የአደጋ ጊዜ ቁጥሮች ጋር በስልክ መዝገብ ጥቂት የመጀመሪያ ገጾች ላይ ይዘረዝራል፡፡ ለምክር ለሌላ መጠለያም ስልክ ልትደውሉ ትቸላላችሁ፡፡ ስማችሁን እንኳን መናገር አያስፈልጋችሁም፡፡
የበጎ አድራጎት ወይም የገንዘብ ድጋፍ ልትፈልጉ ትችላላችሁ፡፡ ቋሚ ነዋሪ ወይም ዜጋ ከሆናችሁ ለበጎ አድራጎት ወይም ለሌላ የገንዘብ ድጋፍ የማመልከት ሕጋዊ መብት አላችሁ፡፡ ካልሆናችሁም በምትኖሩበት ሥፍራ ላይ በመመስረት፣ አሁንም ልታመለክቱ ትችላላችሁ፡፡ ጠቅላይ ግዛቶችና አካባቢዎች ስለገንዘብ ድጋፍ ልዮ ልዮ ሕጎች አሏቸው፡፡ ለምክር ለጠቅላይ ግዛት ወይም አካባቢ ጽሕፈት ቤት ስልክ ደውሉ፡፡
ደጋፊ ያላቸው ስደተኛ የመጀመሪያው የገንዘብ ማግኛ ምንጫችሁ ደጋፊያችሁ ሲሆን፣ ድጋፋችሁ ከተቋረጠ ግን የገንዘብ ድጋፍ ከመንግስት ልታገኙ ትችላችሁ፡፡
በአሁኑ ወቅት በመንግስት በሚደገፍ ስደተኛ ወይም በግል በሚደገፍ ስደተኛ መልክ የገንዘብ ድጋፍ እያገኛችሁ ከሆነ፣ በደል ያለበትን ሥፍራ በመተዋችሁ ድጋፋችሁ አይሠረዝም፡፡ ሕጋዊ መብት እስካላችሁ ድረስ መንግሥት ወይም የግል ድጋፍ ሰጪ ፍላጎታችሁን ማቅረቡን ይቀጥላል፡፡ ስለመብቶቻችሁ ለማወቅና የምትፈልጉትን ድጋፍ ለማግኘት የአካባቢያችሁን የካናዳ ኢሚግሬሽን ማዕክል የግል ደጋፊ ወይም አገልግሎት ሰጪ በግል ጠይቁ፡፡
ለጥበቃ ለማመልከት ወይም ፍቺ ለመጠየቅ ወደፍርድ ቤት ስትሄዱ ፍርድ ቤቱ የልጆቹ አባት ለእናንተና ለልጆቹ የገንዘብ ድጋፍ ክፍያ እንዲያደርግ እንዲዝ ልትጠይቁ ትችላላችሁ፡፡
የፖሊስ ድርጅቱ ጥቃት ደርሶባችኋል የሚል አሳማኝ ምክንያት ካለው በበዳዩ ላይ በወንጀሉ ክስ ሊቀርብበት ይችላል ፡፡ ለፖሊስ ስለበደሉ መናገር ይኖርባችኋል፡፡ ይህን ለማድረግ በቂ ምክንያት እንዳለው ካመነ፣የፖሊስ ድርጅቱ በዳዩን ማረፊያ ቤት ሊያቆየው ይችላል፡፡
በዳዩ ማረፊያ ቤት ከገባ በእሥር ቤት ውስጥ ሊቆይ የሚችለው በፍርድ ቤት በዋስ ቀጠሮ ፍርድ ቤት እስኪ ቀርብ ጥቂት ሰዓት ድረስ ነው ፡፡ ከዚያ በኋላ ፍርድ ቤቱ በእሥር ቤት እንዲቆይ በቂ ምንክያት አለ ብሎ ካልወሰነ በቀር እንዲሄድ ሊፈቀድለት ይችላል፡፡
ስለደህንነታችሁ ከፈራችሁ፣ ይህንኑ በዳዩ ተለቆ ከመሄዱ በፊት ለፖሊስ ድርጅቱ ንገሩት፡፡ ፍርድ ቤቱ በእርሱ መፈታት ላይ ገደቦችን ሊያበጅ ይችላል፡፡ ለምሳሌ፡ ፍርድ ቤቱ በዳዩ ለእናንተ ስልክ እንዳይደውል ወይም እንዳይገናኛችሁ ሊይዝ ይችላል፡፡ እንደገናም ማረፊያ ቤት ሊጨምረው ይችላል፡፡
በሚፈታበት ጊዜ ጉዳት ያደርስብናል ብላችሁ ከፈራችሁ እንደሴቶች መጠለያ የመሣሰሉትን አስተማማኝ ሥፍራዎች ለማግኘት ልትፍልጉ ትችሉ ይሆናል፡፡
በዳዩ በእናንተ ወይም በልጆቻችሁ ላይ ጥቃት የማድረስ ወንጀል መፈጸሙን ካመነ ፍርድ ቤቱ ይፈርድበታል፡፡ ፍርዱም የገንዘብ ቅጣት፣ የሙከራ ጊዜ፣ ዕሥር ቤት የመቆየት ጊዜ ወይም እንዚህን በአንድነት የያዘ ሊሆን ይችላል፡፡ በዳዩ የሙከራ ጊዜው ክፍል የሆነ ሙያዊ ምክር ሊያገኝ ይችላል፡፡ የእሥር ፍርድ አሰጣጡ የመጀመሪያ ጥፋቱ ወይም ደግሞ የበደሉ ክብደት በሚሉት በርካታ ነገሮች ላይ ይመሠረታል፡፡ ከፈራችሁ ይህንኑ ለዘውዱ አቃቤ ሕግ ንገሩት፡፡ የሙከራ ጊዜ ከተሰጠው ፍርድ ቤቱ በፍቺው ላይ ገደቦች ሊያስቀምጥ ይችላል፡፡
በዳይ ወንጀለኛ አይደለሁም ካለ፣ በፍርድ አሰጣጡ ላይ ምስክር መሆን አለባችሁ፡፡ ከበዳይችሁ ጋር እንዳትገናኙ ከእስክሪን በስተጀርባ ወይም ዙረቱ በተገደብ ቴሌቭዥን በሌላ ክፍል ሆናችሁ ምስክርነት እንድትሰጡ ሊፈቀድላችሁ ይችል፡፡ ወይም ደግሞ ምስክርነቱን በምትሰጡበት ጊዜ የበለጠ ዘና እንድትሉ ደጋፊ ሰው ባጠገባችሁ ሊኖራችሁ እንዲችል ይደረጋል፡፡
ፍርዱ የሚጀምረው ከበርካታ ወራት በኋላ ሊሆን ይችላል፡፡ ፍርድ ቤቱ በዳዩን ወንጀለኛ ሆኖ ካገኘው ሊፈረድበት ይችላል፡፡ በጠቅላይ ግዛታችሁ ወይም በአካባቢያችሁ ያለው የዘውድ አቃቤ ሕግ እንዲረዳችሁና የፍርድ ቤቱን ሂደት እንዲገልጽላችሁ ልትጠይቁት ትችላላችሁ፡፡
በዳዩ የካናዳ ዜጋ ከሆነ ከካናዳ ሊወገድ አይችልም፡፡ በዳዩ ስደተኛ ወይም ቋሚ ነዋሪ ከሆነና ፍርድ ቤቱ በጥቃት አድራጊነት ወይም በሌላ የወንጀል ጥፋት ከፈረደበት ሊወገድ ይችላል፡፡ የማስወገዱ ትዕዛዝ ከፍርዱ በኋላ በኢሚግሬሽን ላይ በሚደረግ ቀጠሮ ላይ ይሰማል፡፡ ይሁን እንጂ የማስወግዱ ሂደት ረጅም ጊዜ ሊወስድ ይችላል፡፡
በአደጋ ውስጥ ስትሆኑ፣ በተቻለ መጠን ሥፍራውን በፍጥነት ልቀቁ፡፡ በዚህ ዝርዝር የሚገኙትን ነገሮች ለመሰብሰብ አትቁሙ -- በቀጥታ ሂዱ፡፡ ጊዜ ካላችሁ ግን፣ የምትችሏቸውን ነገሮች ያህል ለመውሰድ ሞክሩ፡፡
ሥፍራውን ለመልቀቅ ካለባችሁና ይህንንም በአፋጣኝ ለማድረግ ከወሰናችሁ ከእናዚህ ጥቂቶቹን ሰብስባችሁ በአስተማማኝ ስፍራ ማስቀመጡ ጥሩ አሳብ ይሆናል፡፡
በቅድሚያ የግል ማኅበረሰብ መጠጊያ ዝርዝር ማዘጋጀት ጥሩ አሳብ ነው፡፡ ከፖሊስ ድርጅት በተጨማሪ ድጋፍ ወይም ጠቃሚ መረጃ የሚሰጡ የተለያዩ ድርጅቶችና ወኪሎች ይገኛሉ፡፡ የሚከተሉትን አካባቢያዊ ወይም የጠቅላይ ግዛት ወኪሎች መገናኛ ቁጥሮችን ለማወቅ የስልክ መዝገባችሁን ነጭ ፣ቢጫ ወይም ሰማያዊ ገጾች ተመልከቱ፡፡ (ከጊዜ ወደ ጊዜ ሊለወጡ ስለሚችሉ፣ እነዚህን ቁጥሮች ወቅታዊ አድርጓቸው)
| ጠቃሚ መጠጊያ | የስልክ ቁጥር |
|---|---|
| የፖሊስ ድርጅት ደህንነታችሁን መገምገም እንድትችሉና ወንጀል በመፈጸም ላይ በሚገኘው ግለሰብ ላይ ክስ እንድትመሠርቱ ሊረዳችሁ ይችላል፡፡ |
(911 ለአደገኛ ሁኔታ) |
| የጉዳት ሰለባ ሙያዊ አገልግሎት ማሕበራት ስለሕግ፣ የሕግ ሥርዓት እና የጉዳት ሰለባዎች ስላሏቸሁ መብቶች አጠቃላይ መረጃ ሊሰጧቸው ይችላሉ፡፡ |
|
| የጉዳት ሰለባ ሙያዊ አገልግሎት ሙያዊ ምክር ወደሚገኝበት በማምራት ለወንጀል ጥቃት ሰለባዎች መርሐ ግብሮችና ሙያዊ አገልግሎቶች ሊነግሯችሁ ይችላል፡፡ |
|
| የችግር ጊዜ መስመሮች ምናልባት በችግር ጊዜ ጣልቃ በመግባት ጠቃሚ ወደሆኑ ሙያዊ አገልግሎት ሊመሩ ይችላሉ፡፡ |
|
| የሽግግር ቤቶች በትዳር ጓደኞቻቸው የጥቃት ሰለባ ለሆኑ ሴቶች መጠለያ፣ መረጃና ሪፈራል ሊያቀርብ የሚችሉ፣ |
|
| የአዕምሮ ጤና ጽሕፈት ቤቶች በክፉ ቀን በድካም ጊዜና፣ እና በአዕምሮ የጤና ችግሮች ላይ መረጃ ወይም ሙያዊ ምክር መስጠት ይችላሉ፡፡ |
|
| የባለ ብዙ ባህሎችና የስደተኞች አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች መረጃ ለመስጠትና ወደጠቃሚ ሙያዊ አገልግሎት ሰጪ ሊያስተላልፉ ይችላሉ፡፡ |
|
| የካናዳ ዜግነት ስደተኝነት በካናዳ የስደተኝነት ደረጃንና ሂደትን በሚመለከት ጥያቄዎችን መመለስ የሚችልና በስደተኞችና ተፈናቃዩች ጥበቃ ሕግ ላይ መረጃ የሚሰጥ፡፡ |
1-888-242-2100 |
| የሕግ ድጋፍ ሙያዊ አገልግሎት በምትኖሩበት ጠቅላይ ግዛት በስደተኝነት በፍትሐብሄር ሕግ ጉዮዳች ላይ ከቤተሰባችሁ ጋር በሕግ ድጋፍ መርሐ ግብር መሠረት ነፃ አገልግሎት ለማግኘት ብቁ ልትሆኑ ትችላላችሁ፡፡ |
|
| የማምናቸው ሰዎች ቤተሰብ፣ ጓደኞች፣ዶክተር ወይም የሃይማኖት አማካሪዎች ሰሜታዊና ተግባራዊ ድጋፍ ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ |
|
| ሌሎች ለእርዳታ ሌሎች መጠጊያዎችን ፈልጉ! ለምሳሌ፡- ከአካባቢ የሴቶች ማዕከል፣ ከማህበረሰብ ጥበቃ ማዕከል እና ወዘተ እርዳታ ልታገኙ ትችላላችሁ፡፡ |